??ጡት ማጥባት??
ጡት ማጥባት በኢትዮጵያ
> ከሚወለዱ ህፃናት ውስጥ ግማሽ ያህሉ(50%) ብቻ እስከ ሁለት አመት ይጠባሉ
> እስከ 6 ወር በትክክል የሚጠቡ(exclusive breast feeding) ህፃናት 52% ናቸው
> ከጡት ተጨማሪ ምግብ(complementary feeding) በወቅቱ(ከ6-9 ወር ባለው ጊዜ) የሚያገኙ ህፃናት 50%ቱ ብቻ ናቸው--->ከነዚህም ውስጥ በትክክልና በአግባቡ የሚያገኙት 4%ቱ ብቻ ናቸው።
አዲስ የተወለዱ ህፃናት በቀን ውስጥ የሚያስፈልጋቸው...
1. ኃይል(energy)--> ከ100-135 ኪሎካሎሪ በኪሎግራም
2. ፕሮቲን---ከ1.5-3.5 ግራም በኪሎ ግራም
NB፦ የተወለዱ ህፃናት የታመሙ እንደሆነ ወይም ከቀናቸው ቀድመው ከተወለዱ ከዚህም በላይ ኃይልና ፕሮቲን ያስፈልጋቸዋል
የእናት ጡት ወተት በውስጡ ያለው ንጥረ ነገር በከፊል...
1. ኃይል--> 67 ኪሎካሎሪ በዴሲሊትር
2. ፕሮቲን--> ከ 1.1-1.3 ግራም በዴሲሊትር
3. ስብ(fat)--> ከ 3.8-4.5 ግራም በዴሲሊትር
4. ካርቦሃይድሬት--> 6.8 ግራም በዴሲሊትር
NB፦ ሲጠቃለል የእናት ጡት ወተት በአግባቡና በትክክል ካጠባን አዲስ ለተወለዱ ህፃናት ለሰውነታቸው አስፈላጊ የሆኑ ንጥረ ነገሮችን ከበቂ መጠን ጋር ይዟል።
የእናት ጡት ወተት ማጥባት ጥቅም
ለልጁ፦
> አዲስ ለተወለደ ልጅ የሚያስፈልገው ንጥረ ነገር በሙሉ በጡት ወተት ስለሚገኝ
> በጡት ወተት የሚገኙ ንጥረ ነገሮች በቀላሉ ስለሚልሙና ወደሰውነት ስለሚሰራጩ( readily absorb and digest)
> የእናትና የልጅን ፍቅር ስለሚጨምር
> የጡት ወተት በውስጡ የተለያዩ በሽታ ተከላካይ ነገሮች(Ig A, complements, bactericidal enzyme...) ስለያዘ በሽታ ይከላከላል
> የአዕምሮ እድገትን ይጨምራል
ለእናት፦
> መዋዕለ ነዋይን(economy) ይቆጥባል
> የእናትነት መንፈስ እንዲሰማ ያደርጋል
> ድህረ ወሊድ መድማትን ይቀንሳል
> የቤተሰብ ምጣኔ እንዲኖር ያደርጋል
> የጡትና የማህፀን በር ካንሰርን ይከላከላል
ትክክለኛ የጡት አጠባብ ዘዴ
1. እናትዮው እንደሚመቻት መቀመጥ/በጎን መተኛት
2. ልጁን ከጀርባው በእጅ መደገፍ
3. የልጁ ጭንቅላትና ሌላው የሰውነት ክፍል ቀጥ እንዲል ማድረግ
4. ልጁና እናትየው ፊት ለፊት መሆን አለባቸው
5. የልጁ ሰውነት ከእናትየው ሆድ ጋር መነካካት አለበት
6. የልጁ አፍ በደንብ መከፈት አለበት
7. የእናትየው የጡት ጫፍ(nipple) ሙሉ በሙሉ በልጅየው አፍ ውስጥ መሆን አለበት
8. የልጁ አገጭ የእናትየውን ጡት መንካት አለበት
ልጁ በደንብ እንደጠባ እንዴት እናውቃለን?
> ከመተንፈሱ በፊት ከ2-3 ጊዜ ጡቱን ይመጠምጣል(suckling)
> ሲጠባ ሁለቱ ጉንጮቹ ስርጉድ(dimpling) ይላሉ
> የጡቱ ወተት በከንፈሩ ይፈሳል
> በየመኃሉ ጥሩ እንቅልፍ ይተኛል
> ቶሎ ቶሎ ይሸናል(በቀን እስከ 6 ጊዜ የሽንት ጨርቅ መቀየር ሊያስፈልግ ይችላል)
> ከተወለደ ከ1 ሳምንት በኋላ በየቀኑ ክብደት ይጨምራል
ጡት ለማጥባት እንደ ችግር
> ወተት መጠራቀም(breast engorgement)
> የጡት ጫፍ መቁሰል/መሰንጠቅ
> የጡት ጫፍ ወደ ውስጥ መግባት(inverted nipple)
> የጡት በሽታ
> የልጅየው ወይም የእናትየው ወይም ሁለቱም መታመም
> እናትየው ተቀጣሪ ሰራተኛ መሆን
ምን እናድርግ?
× ልጅ ሲወለድ ታስቦበትና ታቅዶ እንዲሁም የቤተሰብ ድጋፍ መኖር አለበት
× በእርግዝና ጊዜ በአግባቡ ክትትል ማድረግና የጤና ባለሙያን ምክር መተግበር
× አዲስ የተወለደን ልጅ ሐኪም ከሚያዘው መድኃኒት በቀር እስከ 6 ወር ከእናት ጡት ወተት ውጭ ውሃም ቢሆን አለመስጠት
× ከ6 ወር በኃላ ለስለስ ያሉ ምግቦችን መጀመር
× አዲስ የተወለደን ልጅ ቀንም ማታም ቢያንስ በየ 3ሰአት ልዩነት እንዲሁም ካስፈለገው በማንኛውም ጊዜ ማጥባት
× በምናጠባ ጊዜ አንደኛውን ጡት ጠብቶ ሲጨርስ ብቻ ወደ ሌላኛው ማሻገር
View more on Facebook
This site was designed with Websites.co.in - Website Builder
We appreciate you contacting us. Our support will get back in touch with you soon!
Have a great day!
Please note that your query will be processed only if we find it relevant. Rest all requests will be ignored. If you need help with the website, please login to your dashboard and connect to support