በፌደራል ጤና ሚኒስቴር
የጤና ባለሙያዎች ብቃት ምዘናና ፍቃድ ዳይሬክቶሬት
የብቃት ምዘና ፈተና ለምትወስዱ ጤና ባለሙያዎች በሙሉ
1. የብቃት ምዘና ፈተናው የሚሠጠው ከህዳር 22 እስከ 30/2012 ዓ.ም ሲሆን ፈተናው በሁለት ፈረቃ (ጠዋት እና ከሰዓት በኋላ) የሚሰጥ ይሆናል፡፡
2. የብቃት ምዘና ፈተናው የሚያካትተው ከሰኔ 2011 ዓ.ም ጀምሮ በህክምና፣ ነርሲንግ፣ ጤናመኮንን፣ አንስቴዥያ፣ ፋርማሲ፣ ሜዲካል ላብራቶሪ ቴክኖሎጂ እና ሚድዋይፈሪ ሙያ የተመረቁ ጤና ባለሙያዎችን ነው ፡፡
3. የብቃት ምዘና ፈተናው ከላይ በተጠቀሱት የሙያ መስኮች ከሰኔ 2011 ዓ.ም. በፊት የተመረቁ የጤና ባለሙያዎችን አይመለከትም ፡፡
4. በዚህ የኦንላይን ሲስተም (online system) መመዝገብ የሚችሉት የመጀመሪያውን ዙር ፈተና ወስደው ፈተናውን ያላለፉ ተመዛኞች ብቻ ናቸው ፡፡
5. በዚህ የ online registration system ለመመዝገብ ተመዛኞች የ ኢሜይል(email) አድራሻ ሊኖራቸው ይገባል፡፡ (የኢሜይል አድራሻ የሌላቸው ተመዛኞች የemail account መክፈት ይኖርባቸዋል፡፡)
6. በ online system ለመመዝገብ ተመዛኞች ፎቶ/passport size photo እና መታወቂያ ወይም passport ስካን አድርገው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ፎቶ እና መታወቂያ በሚያስገቡበት ወቅት የፎቶውን/መታወቂያውን መጠን/size መቀነስ (crop ማድረግ) ይኖርባቸዋል፡፡
7. ፈተናውን ለመጀመሪያ ጊዜ የሚወስዱ ተመዛኞች የስም ዝርዝራቸው ከተማሩበት ተቋም በቀጥታ ስለሚላክልን በዚህ ኦን- ላይን ምዝገባ (online registration) መመዝገብ የለባቸውም ፡፡
8. ዳግም ምዘና (Re-exam) የሚወስዱ ተመዛኞች የብቃት ምዘና ፈተናውን መውሰድ የሚፈልጉበትን ከተማ ከተዘረዘሩት አማራጮች ውስጥ መምረጥ ይኖርባቸዋል ፡፡
9. ዳግም ምዘና (Re-exam) የሚወስዱ ተመዛኞች ለፈተናው የተመደቡበትን የፈተና ጣቢያ (assessment center) ከህዳር 1/2012 ዓ.ም ጀምሮ በድረ-ገጽ www.moh.gov.et ወይም በfacebook: Ministry of health, Ethiopia በመግባት መመልከት ይችላሉ፡፡ ፈተናውን ለመጀመሪያ ጊዜ የሚወስዱ ተመዛኞች በቀጥታ የተማሩበት የትምህርት ተቋም በሚገኝበት ከተማ በሚገኝ የፈተና ጣቢያ የሚመደቡ ይሆናል፡፡
10. ተመዛኞች የonline የምዝገባቸውን ካጠናቀቁ በኋላ የምዝገባ መለያ ቁጥራቸውን (Registration ID) መዝግበው መያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
11. ተመዛኞች በምዘና ወቅት እርሳስ፣ መቅረጫና ላጲስ እና ማንነታቸውን የሚገልጽ መታወቂያ ይዘው መገኘት የሚኖርባቸው ሲሆን ከነዚህ ውጪ ሞባይል ስልክን ጨምሮ ማንኛውንም አይነት የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያ ወደ ፈተና ክፍል ይዘው መግባት አይችሉም፡፡
12. የፈተና ፕሮግራሙን ከተማራችሁበት የትምህርት ተቋም እና ከላይ ከተጠቀሱት የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ከህዳር 1/2012 ዓ.ም ጀምሮ ማግኘት ይቻላል፡፡
13. ተመዛኞች ለመመዝገብ ‘YOU DON’T HAVE ACCOUNT, REGISTER NOW’ የሚለውን አረንጓዴ ምልክት በመንካት email እና password ማስባት ይኖርባቸዋል (እስካሁን online ላልተመዘገቡ ብቻ)፡፡
14. የ online ምዝገባቸውን ጀምረው ሳይጨርሱ ያቋረጡ አመልካቾች ምዝገባቸውን ለመቀጠል/ለማጠናቀቅ email እና password አስገብተው sign in የሚለውን ቀይ ምልክት መንካት ይኖርባቸዋል፡፡
15. የ online ምዝገባው ጊዜ እስከ ጥቅምት 16/2012 ዓ.ም የተራዘመ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
16. ተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-5-324185 በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡
· በፌደራል ጤና ሚኒስቴር
የጤና ባለሙያዎች ብቃት ምዘናና ፍቃድ ዳይሬክቶሬት
t.me/yejubietenamerja
View more on Facebook
This site was designed with Websites.co.in - Website Builder
We appreciate you contacting us. Our support will get back in touch with you soon!
Have a great day!
Please note that your query will be processed only if we find it relevant. Rest all requests will be ignored. If you need help with the website, please login to your dashboard and connect to support