የኩላሊት በሽታ ምንድነው?
?? ከባድ የኩላሊት በሽታ በረጅም አመታት ቀስ እያለ ኩላሊታችንን እየጎዳ ከጥቅም ውጪ የሚያደርግ በሽታ ነው። ከጊዜ በኋላ የበሽተኛው ኩላሊት ሙሉ በሙሉ ስራ ያቆማል።
?? ከባድ የኩላሊት በሽታ ወይም ክሮኒክ ኪድኒ ዲዚዝ ሰዎች ከሚያስቡት በላይ በማህበረሰቡ የተንሰራፋ በሽታ ነው። ስር እስኪሰድ ድረስ ለረጅም ግዜ ሳይታወቅ ኩላሊታችንን የሚያጠቃ በሽታ ነው።
?? ኩላሊት ጤናው ወርዶ በ25% ብቃት መስራት ሲጀምር በበሽታው እንደተያዙ ማወቅ የተለመደ ነው። የኩላሊት መስራት ማቆም እየበረታ ሲሄድ ሰውነታችን ውስጥ አደገኛ መጠን ያለው ቆሻሻና ፍሳሽ ይከማቻል። ለዚህ በሽታ ያለው ህክምና የኩላሊትን መዳከም ለማቆም ወይም የሚዳከምበትን ፍጥነት ለማዘግየት የሚሞከርበት ነው። ይህንንም ማድረግ የሚቻለው የበሽታውን መነሻ የሆነውን በሽታ ለማከም እና ለማስታገስ በመሞከር ነው።
#ምልክቶች ምንድናቸው ?
?? ክሮኒክ የኩላሊት በሽታ ቀስ በቀስ ዘግይቶ ኩላሊታችን የሚዳከምበት በሽታ ነው። አንዱ ኩላሊት መስራት ቢያቆምም ሌላኛው ያለ ችግር ሊቀጥል ይችላል። ብዙ ግዜ ህመሙ አሳሳቢ ደረጃ እስኪደርስ እንደታመምን ላናውቅ እንችላለን። ህመም መሰማት ከመረ በኋላ ብዙ ግዜ ጉዳቱን ማከም አይቻልም።
?? ለኩላሊት በሽታ ተጋላጭ የሆኑ ሰዎች በየግዜው የኩላሊታቸውን ጤንነት እየተመረመሩ ማረጋገጥ አለባቸው። በሽታው እንዳለብን በግዜ በማወቅ እራሳችንን ከከባድ የኩላሊት ጉዳት ማዳን እንችላለን።
#የከባድ እኩላሊት ህመም ምልክቶች እንደሚከተለው ናቸው፦
• የደም ማነስ
• ደም የተቀላቀለበት ሽንት
• የጠቆረ ሽንት
• ንቁ አለመሆን
• የሽንት መጠን መቀነስ
• የእግር ፣ የእጅ እና የቁርጭምጭሚት ማበጥ
• የድካም ስሜት
• የደም ግፊት
• እንቅልፍ እጦት
• የሚያሳክክ ቆዳ
• የምግብ ፍላጎት መጥፋት
• ወንዶች ላይ ብልትን ማስነሳት መቸገር
• በሌሊት ቶሎ ቶሎ ለሽንት መመላለስ
• የትንፋሽ እጥረት
• ሽንት ላይ ፕሮቲን መገኘት
• በፍጥነት የሚቀያየር የሰውነት ክብደት
• እራስ ምታት
#የኩላሊት በሽታ ደረጃዎች
• GFR rate የኩላሊት ጤንነት የሚታወቅበት መለኪያ ነው። የGFR rate መጠን የኩላሊታችንን ጤነንት ይናገራል።
?? ደረጃ 1. የGFR መጠናችን ጤነኛ ነው። ቢሆንም ግን የኩላሊት በሽታ እንዳለ ታውቋል።
?? ደረጃ 2. የGFR መጠናችን ከ90 ሚሊ ሊትር በታች ሲሆን ኩላሊታችን ውስጥ በሽታ እንዳለ ታውቋል።
?? ደረጃ 3. የGFR መጠናችን ከ60 ሚሊ ሊትር በታች ነው።
?? ደረጃ 4. የGFR መጠናችን ከ30 ሚሊ ሊትር በታች ነው።
?? ደረጃ 5. የGFR መጠናችን ከ15 ሚሊ ሊትር በታች ነው። የኩላሊት ማቆም አጋጥሟል።
√ አብዛኛው የኩላሊት በሽታ ታካሚ በሽታው ከደረጃ 2 አያልፍበትም። ነገር ግን ህመሙ እንዳይባባስ ህክምና በማድረግ የኩላሊትን ጉዳት መከላከል ተገቢ ነው።
ስኳር በሽታ ያላቸው ሰዎች አመታዊ ህክምና ማድረግ አለባቸው። ሽንታቸው ውስጥ ያለውን የፕሮቲን መጠን በመለካት ኩላሊታቸው አለመታመሙን ማረጋገጥ አለባቸው።
#ህክምናው ምንድነው?
?? ኩላሊት በሽታን የሚያድን መድሃኒት የለም። ነገር ግን የተለያዩ ህክምናዎች በሽታውን ለመቆጣጠር አገልግሎት ላይ ይውላሉ። ከባድ ኩላሊት በሽታ ያለባቸው ሰዎች ብዙ መድሃኒቶችን መውሰድ ይገባቸዋል።
#1ኛ. የደም ማነስ ህክምና
አንዳንድ ደም ማነስ ያለባቸው ኩላሊት በሽተኞች የደም ዝውውር ማድረግ ይኖርባቸዋል። ብዙ ግዜ ግን በሽታው ያለበት ህመምተኛ አይረን ንጥረ ነገር ያላቸውን ክኒኖች መውሰድ ወይንም በመርፌ መልክ ማግኘት ይኖርበታል።
#2ኛ. ፎስፌት ባላንስ
ኩላሊት ህመም ተጠቂዎች ሰውነታቸው በተገቢው ሁኔታ ፎስፌት ማስወገድ ይቸገራል። ታካሚዎች በአመጋገባቸው ላይ ፎስፌት እንዲቀንሱ ይመከራሉ። የወተት ምርቶች ፣ ቀይ ስጋ ፣ እንቁላል እና አሳ ፎስፌት ስለያዙ አይመከሩም።
#3ኛ. የደም ግፊት
የኩላሊት በሽታ ተጠቂ የሆኑ ሰዎች ብዙ ግዜ ደም ግፊታቸው ከፍተኛ ነው። ኩላሊትን ለመጠበቅ ደም ግፊትን መቆጣጠር ያስፈልጋል።
#4ኛ. ቆዳ ማሳከክ
እንደ ክሎሮፌናሚን አይነት መድሃኒቶች የቆዳን ማሳከክ ያስታግሳሉ።
#ህመምን የሚያስታግሱ መድሃኒቶች
ኩላሊት መስራት ሲያቆምና ሰውነት ውስጥ መርዛማ ንጥረ ነገሮች ሲከማቹ ታካሚው የማቅለሽለሽ ወይም የመታመም ስሜት ይሰማዋል። በዚህ ግዜ እንደ ሳይክሊዛይን አይነት መድሃኒቶች ህመምን ያስታግሳሉ።
#የመጨረሻ ደረጃ ህክምናዎች
ኩላሊት አቅሙ ተሟጦ በ10 - 15 ፐርሰንት ደረጃ መስራት ሲጀምር ከላይ የተዘረዘሩት ህክምናዎች ብቻቸውን በቂ አይሆኑም። የመጨረሻ የኩላሊት ደረጃ የደረሱ ታካሚዎች ሰውነታቸው ውስጥ የሚከማቸውን ቆሻሻ እና ፈሳሽ ያለ እገዛ መቋቋም አይችሉም። ታካሚው በህወት ለመኖር ዳያሊሲስ ያስፈልገዋል።
ኩላሊት መጨረሻው ደርሶ አስፈላጊ ካልሆነ ዶክተሮች ዳያሊሲስ እና ንቅለ ተከላን ለማድረግ አይመርጡም። እነዚህ ህክምናዎች በኢንፌክሽን ምክንያት መወሳሰብ ሊፈጥሩ ይችላሉ።
#ዳያሊሲስ ምንድነው?
?? ዳያሊሲስ በማሽን የሚደረግ የሰውነት ቆሻሻን ማጥራት ስራ ነው። ሁለት አይነት የዳያሊሲስ አይነት አለ። አንደኛው ሂሞዳያሊሲስ ነው።
?? ይህ የዳያሊሲስ አይነት ደም ከሰውነታችን ፓምፕ እየተደረገ በማሽን ውስጥ አልፎ እየተጣራ እንዲገባ የሚደረግበት ህክምና ነው። 3 ሰአት የሚፈጅ ህክምና ነው። ህክምና ባለሙያዎች እንደሚሉት ይህን ህክምና በተደጋጋሚ ማድረግ ለታካሚው ጤና ጥሩ ነው።
?? ሌላኛው የዳያሊሲስ አይነት ፔሪቶኒያል ዳያሊሲስ ሲሆን የታካሚው ደም በራሱ ሆድ ውስጥ እንዲጣራ ይደረጋል። ሆድ ውስጥ በሚገባ ካቴተር ውስጥ የዳያሊሲስ ውህድ በመጨመር ቆሻሻ እና ፍሳሽ እንዲወጣ ይደረጋል።
#የኩላሊት ንቅለ-ተከላ
ከኩላሊት መስራት ማቆም በቀር ሌላ ኩላሊትን የሚጎዳ በሽታ ለሌላቸው ታካሚዎች ኩላሊት ንቅለ - ተከላ ከዳያሊሲስ የተሻለ አማራጭ ነው። ቢሆንም ግን ንቅለ - ተከላ ከማድረጋቸው በፊት ታካሚዎች የዳያሊሲስ ማሽን እርዳታ ያስፈልጋቸዋል።
?? ኩላሊት ለጋሹ እና ተቀባዩ ተመሳሳይ የደም አይነት ፣ የሴል ሰርፌስ ፕሮቲን እና አንቲቦዲ ሊኖራቸው ይገባል። ካልሆነ የተቀባዩ ሰውነት ኩላሊቱን ላይቀበለው ይችላል። ብዙ ግዜ የዘመድ ግንኙነት ያላቸው ሰዎች የተሻለ ለጋሽ ይሆናሉ።
?? t.me/yejubietenamerja
View more on Facebook
This site was designed with Websites.co.in - Website Builder
We appreciate you contacting us. Our support will get back in touch with you soon!
Have a great day!
Please note that your query will be processed only if we find it relevant. Rest all requests will be ignored. If you need help with the website, please login to your dashboard and connect to support