X

By Abebaw Mebratu
Mon, 21-Oct-2019, 10:40

ወባ በሽታ (malaria) ምንነት > የወባ በሽታ በሴቷ የወባ ትንኝ በሚተላለፍ ''ፕላዝሞዲዬ...

ወባ በሽታ (malaria) ምንነት > የወባ በሽታ በሴቷ የወባ ትንኝ በሚተላለፍ ''ፕላዝሞዲዬም/plasmodium'' አሀዱ ህዋስ አማካኝነት የሚመጣ በወቅቱ ካልታከመ ለህይወት አስጊ የሆነ በሽታ ነው። > በአገራችን ኢትዮጵያ በብዛት በፀደይ/በልግ እና በክረምት ወቅት በብዛት ይከሰታል። መነሻ(Etiology) ሀ. ፕላዝሞዲዬም ፋልሲፋረም(Plasmodium Falciparum) ለ. ፕላዝሞዲዬም ቫይቫክስ(P. Vivax) ሐ. ፕላዝሞዲዬም ኦቫሊ(P. Ovale) መ. ፕላዝሞዲዬም ማላሪ(P. Malariae) ሠ. ፕላዝሞዲዬም ኖለሲ(P. Knowlesi) አጋላጭ ምክንያቶች > ሞቃትና ደረቃማ(በረሃማ) አካባቢዎች/tropical area ላይ መኖር (ለምሳሌ፦ ከሰሃራ በታች ያሉ የአፍሪቃ አገሮች) > በአካባቢ የታቆረ ውሃ መኖር > ከዚህ በፊት በወባ በሽታ መያዝ (በተለይ P.Vivax እና P. Ovale) > ወባ በሽታ በብዛት በሚከሰትባቸው አካባቢዎች መጓዝ > እርጉዝ እና ህፃናት ምልክቶች > ከፍተኛ የሆነ የሰውነት ሙቀት > ሰውነትን ማንቀጥቀጥ > ብርድ ብርድ ማለት > መገጣጠሚያን መቆርጠም(በተለይ ከጀርባና ጉልበት) እና የጡንቻ ህመም > ሳል ማሳል > ድካም/የሰውነት መዛል > የምግብ ፍላጎት መቀነስ > ማቅለሽለሽና ማስመለስ ጠንቅ(complication) > ደም ማነስ(anemia) > የሰውነት ስኳር መጠን መቀነስ(hypoglycemia) > የጭንቅላት ወባ(cerebral malaria) > የኩላሊት መድከም(renal failure) > ሳንባ ላይ ውሃ መቋጠር(pulmonary edema) ፧ ምርመራ > የደም ምርመራ > የስኳር መጠን ምርመራ > የኩላሊት ምርመራ . > የደረት ራጅ > የጉበት ምርመራ ህክምና > የሙቀት ማስታገሻ መድኃኒት > እንደ ፕላዝሞዲዬም አሀዱ ህዋስ አይነት የሚዋጥ እንክብል መድኃኒት > በመድፌ የሚሰጥ መድኃኒት(በሽታው ከፍተኛ/ጠንቅ ያለው ከሆነ) ምን እናድርግ? > በአካባቢያችን ውሃ ያቆሩ ኩሬዎችን ፀረ ወባ መድኃኒት መርጨት ወይም ማፋሰስ > በፀረ ወባ ኬሚካል የተነከረ አጎበር መጠቀም > ወባ ወደሚበዛባቸው አካባቢዎች ስንሄድ መከላከያ መድኃኒት(antimalaria chemoprophylaxis) መውሰድ > ከላይ የተጠቀሱ ምልክቶች ሲኖሩ ወደ ጤና ተቋም መሄድ

View more on Facebook

This site was designed with Websites.co.in - Website Builder

WhatsApp Google Map

Safety and Abuse Reporting

Thanks for being awesome!

We appreciate you contacting us. Our support will get back in touch with you soon!

Have a great day!

Are you sure you want to report abuse against this website?

Please note that your query will be processed only if we find it relevant. Rest all requests will be ignored. If you need help with the website, please login to your dashboard and connect to support