ኤዲስ(AIDS)
ምንነት
> ኤዲስ HIV(human immunodeficiency virus) በተባለ በሽታ አምጭ ተህዋሲያን አማካኝነት የሚመጣ ከሰው ወደ ሰው ተላላፊ የሆነ በሽታ ነው።
> በ 2015 እኤአ በተደረገ ጥናት በአለም ላይ 36.7 ሚሊዮን ህዝብ በኤድስ የተያዘ ሲሆን 1.1 ሚሊዮን ህዝብ ደግሞ ሞቷል። በኤድስ በሽታ ከተያዙት ውስጥ አብዝሃኛውን የያዙት ከሰሀራ በታች ባሉ የአፍሪቃ አገሮች ነው።
> ወንድ ከወንድ በሚደረግ ግብረ-ስጋ ግንኙነት(Gays) በ 28 እጥፍ በኤዲስ ይጠቃሉ።
መተላለፊያ መንገዶች
> ልቅ በሆነ ግብረ-ስጋ ግንኙነት
> ስለታም ነገሮችን አብሮ በመጠቀም
> ከእናት ወደ ልጅ
አጋላጭ ነገሮች
> ልቅ የሆነ ግብረ ስጋ ግንኙነት መኖር
> ስለታም ነገሮችን(መርፌ፣ ምላጭ፣ መቀስ...) በጋራ መጠቀም
> የአባላዘር በሽታ ተጠቂ መሆን
> ከደም ጋር ንክኪ መኖር
> ሴተኛ አዳሪ መሆን/sex tourism
> በቫይረሱ ከተያዘች እናት ወደ ልጅ
ምልክቶች፦ የራሱ የሆነ typical ምልክት የለውም
> የሰውነት ሙቀት፣ ማንቀጥቀጥ፣ የሰውነት መቆሳሰል፣ ሳል፣ የጉሮሮ ህመም...(acute seroconversion stage)
> አንገት፡ ብብትና ንፍፊት/inguinal... አካባቢ ማበጥ(lymphadenopathy)
> የምግብ ፍላጎት መቀነስ፣ ምክንያቱ የማይታወቅ የክብደት መቀነስ፣ መክሳት፣ ለረጅም ጊዜ የቆየ ተቅማጥ(HIV wasting Syndrome)
> አዕምሮ መሳት/መዘንጋት(AIDS associated dementia/encephalopathy
> የተጓዳኝ በሽታዎች ምልክት(የሳንባ በሽታ/TB, PCP/ ፣ የጉሮሮና የአፍ ፈንገስ፣ የልብ በሽታ፣ የኩላሊት በሽታ፣ የጭንቅላት በሽታ...)
ምርመራ
> የደም ምርመራ
> የCD4+ ምርመራ
> የሽንትና የሰገራ ምርመራ
> የኩላሊትና የጉበት ምርመራ
> የአክታ ምርመራ፣ የደረት ራጅ
ህክምና
> ART(HAART)
> የተጓዳኝ በሽታዎች ህክምና
> የ PCP, mycobacterium avium, CMV...ቅድመ መከላከል(Prophylaxis)
ምን እናድርግ?
× ሦስቱን የ"መ" ህጎች ብናከብር(መታቀብ/ከጋብቻ በፊት sex አለማድረግ/፣ መወሰን/አንድ ለአንድ ተወስኖ መኖር/፣ መጠቀም/sex ማድረግ ካልቀረ ኮንዶም መጠቀም/)
× ጋብቻ ከመፈፀማችን በፊት ራሳችንን ብናውቅ/የ HIV ምርመራ ብናደርግ
× ቫይረሱ በደሟ ያለ እናት ወደ ልጇ እንዳይተላለፍ በጤና ተቋም የእርግዝና ክትትል ብታደርግና የምክር አገልግሎት ብታገኝ
× ራሳችንን ከማንኛውም አደንዛዥ ሱስ(ጫት፣ አልኮል፣ ሲጋራ..) ብንጠብቅ
× ምንግዜም ግብረ-ስጋ ግንኙነት ስናደርግ ኮንዶም ብንጠቀም
× ከላይ የተጠቀሱ አጋላጭ ነገሮችን ብናስወግድ
× በየ 3ወሩ በመመርመር ራሳችንን ብናውቅ
× ቫይረሱ በደማችን ካለ እንደማንኛውም ሰው መኖር እንደምንችል አውቀን መድኃኒቱን ሳናቋርጥ በትክክል ብናደርግ እንዲሁም በቀጠሮ ክትትል ብናደርግ
× ማንኛውንም የምክር አገልግሎት ስንሻ ወደ ጤና ተቋም ብንሄድ
View more on Facebook
This site was designed with Websites.co.in - Website Builder
We appreciate you contacting us. Our support will get back in touch with you soon!
Have a great day!
Please note that your query will be processed only if we find it relevant. Rest all requests will be ignored. If you need help with the website, please login to your dashboard and connect to support